አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2017(ኢዜአ)፦ ጅግጅጋ ለሶማሌ ክልል ከተሞች ሞዴል በሚሆን መልኩ ሰፊ የልማት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የጅግጅጋ ከተማን የኮሪደር ልማት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት የምስራቋን ኮከብ ወርቃማ የውበት ደባብ አልብሷታል ብለዋል።
በከተማዋ በምሽት ተዘዋውረው ባደረጉት ምልከታ ከስምንት ወራት በፊት በሁለት ምዕራፍ የተጀመሩ ስራዎች በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።
የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን የአስፋልት መንገዶች ያሰፋ፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችንም ያካተተ መሆኑን አድንቀው፥ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውም ገልጸዋል።
የወጣቶችና ታዳጊዎች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችም በመገንባት ላይ ናቸው ብለዋል።
ከተማዋ ለክልሉ ከተሞች ሞዴል በሚሆን መልኩ ሰፊ የልማት ጎዳና ላይ መሆኗንም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።
የከተማዋ የቆየ ችግር የነበረውን ጎርፍ መከላከል የሚያስችሉ ማፋሰሻዎች፤ የተቀናጀ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮምና የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች የሚያበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ባለሀብቶች በከተማዋ በሆቴል አገልግሎትና ሌሎች ዘርፎች ተሰማርተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ ይገኛሉም ነው ያሉት።
በጅግጅጋ ከተማ በሁለት ምዕራፍ የ30 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ለማከናወን ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025