የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የምግብ ስርዓት ጉባዔ ተሳታፊዎች ማዕከሉን መጎብኘታቸው ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል

Jul 30, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 20/2017(ኢዜአ)፦የሁለተኛው የተመድ የምግብ ስርዓት ጉባዔ ተሳታፊዎች ማዕከሉን መጎብኘታቸው ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ደቻሳ ገለጹ።

በኢትዮጵያ፣ በጣልያን እና በተመድ ትብብር የተዘጋጀው ሁለተኛው የተመድ የምግብ ስርዓት ጉባኤ እስከ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ከተለያዩ አገራት የመጡና የሁለተኛው የመንግስታቱ ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከልን ጎብኝተዋል።

የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ደቻሳ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት ስር ከሚገኙ 22 የምርምር ማዕከላት አንዱ ነው።

የምርምር ማዕከሉ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት ከዳር ለማድረስ ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ እንደገለጹት፤ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ መነሻነት ማዕከሉ መጎብኘቱ በግብርናው ዘርፍ የሚደረገውን ትብብር ያጠናክራል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.