አዲስ አበባ፤ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ):-የኮሪደር ልማቱ ባህር ዳር ከተማን ካላት የተፈጥሮ መስህብ ጋር ማስተሳሰር ማስቻሉን የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በበጀት አመቱ በከተማው ለየት ባለ መልኩ ሁለት መሰረታዊ ግቦችን ለማሳካት ተሰርቷል።
በዚህም የመጀመሪያው የከተማውን እና የአካባቢውን ሰላም ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸው ፤ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
ከከተማው ነዋሪ ህብረተሰብ ጋር በተደረጉ ውይይቶችም የከተማውን ነዋሪ የሰላም ባለቤት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው፤ በዚህም የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።
ትልቁ ስኬት ተደርጎ የሚወሰደው ከዚህ ቀደም ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች በጥራት እና በፍጥነት መጠናቀቃቸው መሆኑንም ገልጸዋል።
ሌላኛው በከተማው ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራው የኮሪደር ልማት መሆኑንና ይህም የከተማዋን ውበት በሚጨምር መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።
የከተማዋን ፕላን ከተፈጥሮ ጋር መስተጋብር ያልተፈጠረበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰዋል።
የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ከተፈጥሮ ጋር ያላትን መስተጋብር በማገናኘት ተጨማሪ ውበት መፍጠሩንና ተፈጥሮን አጉልቶ ማሳየት ማስቻሉን በመግለጽ።
በኮሪደር ልማቱ ላይ የተከናወኑ መሰረተ ልማቶች በተቀናጀ መንገድ በመሬት ውስጥ መዘርጋታቸውን ጠቁመዋል።
በሁለተኛው ምእራፍ የኮሪደር ልማት 5 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህም 2 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የማጠናቀቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ የቱሪስት መናሀሪያነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተጨማሪም የፋይል ዲጂታላይዜሽንን ጨምሮ የከተማዋን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ከፍ ያደረጉ የአሰራር ስርዓቶች ተዘርግተው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በባህር ዳር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የብልጽግና ጉዞዎችን ትክክለኛ ማሳያ መሆናቸውን ገልጸው፤ የፌደራል መንግስት ለከተማዋ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ስራዎችን እየተከታተለ መሆኑንም ተናግረዋል።
ይህም የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማስቻሉን ጠቅሰው፤ ለተገኙ ስኬቶች ህብረተሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ገልጸዋል።
በቀጣይም በተጀመረው አግባብ ከተማዋን የማስዋብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025