አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/ 2017 (ኢዜአ)፦ በ2017 በጀት ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከህብረተሰቡ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በፋይናንስ በኩል በራስ አቅም በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባ መሆኑም ተገልጿል።
በ2017 በጀት ዓመት ህብረተሰቡ ለግድቡ ግንባታ ያደረገውን ድጋፍ፣ ትብብርና እገዛ በተመለከተ የጽህፈት ቤቱ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ፍቅርተ ተአምር ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህ ወቅት ከቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ ከ8100 A አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ከፒን ሽያጭና ከሌሎች መንገዶች ገቢ ማሰባሰብ ማቻሉን ተናግረዋል።
በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለግድቡ ግንባታ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ድጋፍ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
ይህም ከዕቅድ አንጻር የ7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ምክትል ስራ አስፈፃሚዋ አስታውቀዋል።
ፕሮጀክቱ በፋይናንስ በኩል በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ መቶ በመቶ በራስ አቅም የተገነባ መሆኑን ገልጸው፤ መላው ኢትዮጵያዊ በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበትና ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጨምሮ በአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ የተመዘገበ ስኬት መሆኑንም አስረድተዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025