
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2017(ኢዜአ)፦የመንገድ መሰረተ ልማትን ከተለያዩ ዘርፎች ጋር ማስተሳሰር ለፈጣን ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ::
ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በትራንስፎርሜሽን ሊደርሺፕ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው ።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ስልጠናውን መስጠት በጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት መንገድ ለአንድ አገር እድገት እና ብልጽግና ወሳኝ ነው፡፡
የመንገድ ግንባታ ኢኮኖሚን በማሳለጥ፣ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት አንድን አገር ከድህነት ለማውጣት በሚሰራው ስራ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል፡፡
የመንገድ ግንባታ አገልግሎትን ከተገልጋይ በማገናኘት፣ ማህበራዊ አካታችነትን በተግባር በማረጋገጥ በኩል ትልቅ ሚና እንዳለውም አንስተዋል።
የመንገድ ሃይሎች የታሰበላቸውን ውጤት እንዲያስገኙ በተለይ ከዲዛይን እስከ ግንባታ እንዲሁም አጠቃቀሙ ላይ ማተኮር ይገባል ነው ያሉት፡፡
በተለይ እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ ንግድ እና ከሌሎች ዘርፎች ጋር በሚገባ የመንገድ ግንባታን ማስተሳሰር ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊ ኢንጂነር አብረሃም አብደላ መንገድ ከምህንድስና አንጻር ብቻ ሳይሆን ከሰዎች ሕይወት ጋር ያለውን መስተጋብር ለመረዳት የቻሉበት ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

መንገዶችን ስንሰራ አንድ አካባቢን ከሌላው ጋር ከማገናኘት ባለፈ ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች አልቆ መገንዘብ እንደሚገባ ከስልጠናው የተገነዘቡበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ኢንጂነር አንድነት ሰይፉ ናቸው፡፡
ሰልጣኞቹ የተሰጠው ስልጠና ከሙያዊ እይታ ባሻገር ለአገር ከሚያስገኘው ፋይዳ ጋር አስተሳስሮ ማየት አስችሎናል ብለዋል።

ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የትራንስፎርሜሽን ሊደርሺፕን በተመለከተ ስልጠና ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025