አዲስ አበባ፤ሐምሌ 7/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ኤክስፖርት እና ኢምፖርት ባንክ(አፍሪ ኤግዚም ባንክ) ለአፍሪካን የልማት እና ትስስር ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ።
47ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት እና 7ኛው የህብረቱ ቀጣናዊ ማህበረሰቦች የመንፈቅ ዓመት የጋራ የትብብር ስብሰባ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ተካሂዷል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተሰናባቹ የአፍሪካ ኤክስፖርት እና ኢምፖርት ባንክ(አፍሪ ኤግዚም ባንክ) ተሰናባች ፕሬዝዳንት እና የቦርድ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ቤኔዲክት ኦርማህ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪ ኤግዚም ባንክ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጎልበትና ባንኩ ለአፍሪካ ልማት እና ትስስር የሚያደርገውን ድጋፍ የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ሊቀ መንበሩ ባንኩ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከልን ጨምሮ ለአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራትና ለኮሚሽኑ እያደረገ ያለውን ዘላቂ ድጋፍ አድንቀዋል።
በተጨማሪም ሊቀ መንበሩ ከአዲሱ የባንኩ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ኢሎምቢ(ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025