
ጅማ፣ ሰኔ፣30/2017(ኢዜአ) ፡- በኦሮሚያ ክልል የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት ለስራ እድል ፈጠራ ትኩረት መስጠቱን የክልሉ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ።
የኦሮሚያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ዛሬ በጅማ ከተማ የኢንተርፕራይዞች ሽግግር እና እውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በክልሉ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ ዳይሬክተር አቶ ተማም ሁሴን እንዳሉት በክልሉ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
ወጣቶቹ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደራጅተው ወደ ስራ የሚገቡበትን፣ የማምረቻ፣ የመሸጫ፣ የገበያ ትስስርና የብድር አገልግሎት በማመቻቸት ኢኮኖሚያዊ ሽግግር እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ዛሬም የጅማ ከተማ፣ ጅማ ዞን፣ አጋሮ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር እና መቱ ከተሞች የሚገኙ 120 የሚሆኑ ማህበራት ወደ ኢንቨስትመንት መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።

የጅማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር አስራት እሸቱ በበኩላቸው በከተማዋ በርካታ የስራ እድሎች እየተፈጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በከተማዋ ልማትን በማፋጠን የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በተለይ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ቅድሚያ መሰጠቱን ገልጸዋል።
መንግስት የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ከሚሰጣቸው አቅጣጫዎች አንዱ ወጣቱን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር ናቸው።
በዞኑ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ገልጸው ይህም የወጣቶችን የኢኮኖሚ አቅም የሚያጎለብት ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የ'መልካሙ ሀይሌና አዱኛ የህንጻ' ግንባታ ስራ ማህበር አባል ወጣት ዮናስ ታረቀኝ እንዳለው ተደራጅተው በጀመሩት የግንባታ ስራ ተጠቃሚነታቸው በማደጉ ወደ ኢንቨስትመንት መሸጋገራቸውን ጠቁመዋል።
ሌላው በማህበር ተደራጅተው እየሰሩ ከሚገኙ ወጣቶችም መካከል መለሰ እና ጓደኞቹ የመንገድ ስራ ማህበር አባል ወጣት ሮባ ለገሰ በበኩሉ ተደራጅተው አነስተኛ የመንገድ ስራዎች በመስራት ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሌሎች ወጣቶችም ስራ በመፈለግ ጊዜያቸውን ከማባከን ይልቅ በመረጡት የስራ ዘርፍ በመደራጀት ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አስረድተዋል።
የክልል፣ የከተማና የዞን አስተዳደር አካላትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...
Apr 14, 2026
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025