
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ አዲስ በረራ ጀምሯል።
አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ በሣምንት አራት ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
አየር መንገዱ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ ከተማ የሚያደርገውን በረራ አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን የማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተከናውኗል።
በመርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ፥ አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ የሚያደርገው በረራ ፖርቹጋልን ከአፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ መንገደኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለውም ነው የገለጹት።
በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ የጀመረው በረራም የሀገራቱን ወዳጅነት በኢኮኖሚና ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር እንደሚያግዝም አውስተዋል።
አየር መንገዱ ዛሬ ያስጀመረውን በረራ ጨምሮ ከ145 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግና በዓመት 67 ሚሊዬን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል።
ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...
Apr 14, 2026
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025