አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ)፦ ምንም አይነት የነዳጅ የዋጋ ጭማሪም ሆነ የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ምንም አይነት የነዳጅ አቅርቦት እጥረት አለመኖሩን አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በቂ ነዳጅ በየጊዜው እየገባ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ነገር ግን በስግብግብ ነጋዴዎች ምክንያት የነዳጅ እጥረት እንዳለ ለማስመሰል ሙከራ መደረጉን ገልጸዋል።
ይህን ባደረጉ ሁለት የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመው፤ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025