ቦዲቲ፤ግንቦት 30/2017 (ኢዜአ)፦በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ እየተከናወነ ያለው የተቀናጀ የኮሪደር ልማት በሌሎች ከተሞች ላይ ተከናውኖ ያየነውን ውጤት በከተማችንም ተፈፃሚ ሆኖ ለማየት ስንመኘው የነበረ የልማት ስራ ነው ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ከ12 ኪሎ ሜትር በላይ የተቀናጀ የኮሪደር ልማት ስራን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በከተማው ኢዜአ ካነጋገራቸው ነዋሪዎች መካከል አቶ ተሾመ አካኮ፥ የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ከማሳመር ባለፈ የስራ ዕድልን ፈጥሯል ብለዋል።
በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅና ልማቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ድጋፋቸውን እንዲሚያጠናክሩም ተናግረዋል።
ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ፈቃዱ ጌታ በበኩላቸው፥ በሌሎች አካባቢ አይተውት ሲመኙት የነበረው የኮሪደር ልማት በከተማቸው በመጀመሩ መደሰታቸው ገልጸዋል።
የልማት ስራው በእድገት ላይ የሚትገኘውን የቦዲቲ ከተማን ተጨማሪ ውበትን እያጎናጸፋት እንደሚገኝ ገልፀው፥ ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው በሚችሉት ነገር ሁሉ ለመደገፍ መዘጋጀታቸውንም ነው አስተያየት ሰጪው የገለጹት።
የቦዲቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መዝገቡ ሞሬቦ፥ በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እያሳየ መሆኑን ገልጸው፥ ለስራው ስኬታማነት የከተማው ነዋሪዎች ላሳዩት ትብብር አመስግነዋል።
ከተማውን አቋርጦ በሚያልፈው አስፖልት መንገድ ግራ እና ቀኝ ከ12 ኪ. ሜ በላይ የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ስራውን የከተማ አስተዳደሩ ከነዋሪውና ከባለሀብቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አመልክተው፥ ለስራው ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መመደቡንም ጠቁመዋል።
በከተማው የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ከግብ ለማድረስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የቦዲቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የመሬት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮናታን ሳሙኤል ናቸው።
በከተማው በተለዩ ዘጠኝ ስፍራዎች የኮሪደር ልማት ስራ እንደሚከናወን ገልጸው፥ ስፍራዎቹን ምቹ የማድረጉ ተግባር ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
በከተማው እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማውን ውብና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድልን ያመቻቸ መሆኑም ተመላክቷል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025