ጎንደር፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከምግብ ፎጆታ ባለፈ የኢኮኖሚ አቅም እየፈጠረላቸው መሆኑን በጎንደር ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ ሴቶች ተናገሩ፡፡
በጎንደር ቀጠና የሚገኙ ሴት አመራሮች በከተማው በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ሞዴል በሆኑ ሴቶች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራትን በተመለከተ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
በዘርፉ ከተሰማሩ ሞዴል አልሚዎች መካከል ወይዘሮ ጽላተማርያም ተመስገን፤ በ50ሺህ ብር ካፒታል የጀመሩት የዶሮ እርባታ አሁን ላይ ወደ ሚሊዮን መሸጋገሩን ተናግረዋል።
በአራት የዶሮ ፋርሞች ከ65ሺህ በላይ ዶሮዎች እንዳሏቸው ጠቅሰው በልማቱ ከራሳቸው አልፈው ለብዙዎች የስራ እድል መፍጠራቸውንና ጥሩ የኢኮኖሚ አቅም እንዲገነቡ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
ወጣት ከበቡሽ ምስጋናው በዶሮ አርባታ እንዲሁም ወይዘሮ እስከዳር ብርሃኑ በወተት ላሞች እርባታ ስኬታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ከምግብ ፎጆታ ባለፈ ለብዙዎች የኢኮኖሚ አቅም እየፈጠረ መሆኑን አልሚዎቹ ገልጸዋል።
የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ፤ በከተማው ከ50 በላይ ኢንተርፕራይዞች በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተሰማርተው እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት በ60 ሚሊዮን ብር ወጪ ለዶሮ እርባታ ስራ የሚውሉ የክላስተር ሼዶችን በመገንባት ለስምንት ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፉን ጠቅሰዋል።
የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ፤ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በተለይም የሴቶችን የምጣኔ ሃብት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በርካታ ሴት ባለሀብቶችን ለማፍራት ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ጠቁመው የልምድ ልውውጡ አላማም የሴቶች ተሳትፎና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማጎልበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025