ሐረር፤ ግንቦት 1/2017(ኢዜአ)፦ ዩኒቨርሲቲዎች ሀገር በቀል እውቀቶችን በማልማትና በማበልጸግ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት ጥቅም እንዲውሉ መስራት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሪክተር ወልዱ ይመስል ተናገሩ።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማህበራዊና የምጣኔ ሃብት ጠቀሜታ ለማዋል የማልማትና የማበልጸግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ጠቀሜታ ያላቸው ሀገር በቀል እውቀቶች ቢኖሩም እስካሁን እምብዛም ጥቅም ላይ ሳይውሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ሀገር በቀል እውቀቶችን በማልማትና በማበልጸግ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት ጥቅም እንዲውሉ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን እምቅ ሀገር በቀል እውቀቶች ለሀገር ልማትና እድገት እንዲሁም ለዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪነት መጠቀም ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት ይስሃቅ የሱፍ(ዶ/ር)፤ በዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀቶችን ከመመዝገብና ከማደራጀት ባለፈ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማህበራዊና የምጣኔ ሃብት ጠቀሜታ ለማዋል የማልማትና የማበልጸግ ስራን አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
በእውቀት የታነፀ ትውልድ ከማፍራት ባለፈ የግብርና አሰራር፣ ግጭት አፈታት፣ ባህላዊ እውቀቶችና ሌሎች ለሀገር ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሀገር በቀል እውቀት አስተባባሪ ያስሚን መሀመድ፤ ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀቶችን የመሰነድ፣ የማዳበርና ክህሎትን የማሳደግ ስራ በትኩረት እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025