አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 18/2017(ኢዜአ)፦ዓለም አቀፉ የአብራሪዎች ቀን (World Pilots’ Day) ዛሬ እየተከበረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት የዛሬው ቀን የአየር መንገዱ የስኬት እና የጀግንነት ተምሳሌት ለሆኑት አብራሪዎች ክብር የምንሰጠበት ነው ብሏል።
አብራሪዎች በክህሎታቸው፣ በታታሪነታቸው እና በጠንካራ የጸና መንፈስ የአፍሪካን ህልሞች ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይዞ በመጓዝ ሀገራትን፣ ባህሎች እና እድሎችን በማስተሳሰር ቁልፍ ሚና እየተወጡ ነው ብሏል።
ዛሬም ሁልጊዜም እናከብራችኋለን ሲል ገልጿል አየር መንገዱ ባስተላለፈው መልዕክት።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025