አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2017(ኢዜአ)፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር በዘላቂ ልማት እና እድገት ላይ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎቶች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር እና የተመድ ረዳት ዋና ፀሐፊ ሆርጌ ሞሬራ ዳ ሲልቫ ከገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ጋር ተወያይተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ከሚኒስትሩ ጋር ጽህፈት ቤቱ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት የግዢ ስርዓት እና የመልሶ መቋቋም ስራዎችን ጨምሮ ጽህፈት ቤቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ጽኑ እና የዘላቂ እድገት አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025