
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ በተቋቋመው የተባበሩት መንግስታት የዲጂታል ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ቢሮ (UN-ODET) አባል ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ ተቋማዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የተመድ ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የቢሮው ልዩ ልዑክ አማንዲፕ ሲንግ ጊል (ዶ/ር) ገለጹ።
በአማንዲፕ ሲንግ ጊል (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልዑኩ አቀባበል አድርገዋል።
ሁለቱ ወገኖች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት እና ትግበራ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል።
ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልዑኩ ኢንስቲትዩቱ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን መሰረት በማድረግ እየተገበራቸው ያሉ ኢኒሼቲቮችን አስመልክቶ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የመፍትሄ አማራጮች እና ኢኒሼቲቮች መጠቀም የሚያስችለውን የጋራ ትብብር ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና በድርጅቱ በተቋቋመው አዲስ የዲጂታል ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ቢሮ (UN-ODET) ልዩ ልዑክ አማንዲፕ ሲንግ ጊል (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በአጭር ጊዜ በኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት ላይ የመጣውን ከፍተኛ ለውጥ አድንቀዋል።
ተቋሙ በድርጅቱ በተቋቋመው አዲስ የዲጂታል ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ቢሮ (UN-ODET) አባል የመሆን ጠንካራ አቅም እንዳለው መግለጻቸውን የኢኒስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025