አዲስ አበባ፤መጋቢት 10/2017(ኢዜአ):- ሀገር በቀል እውቀቶችን ከፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር አሰናስሎ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ።
ሚኒድትሯ፥ ከማፊ ፋሽን ዲዛይን መሥራች ወ/ሮ ማህሌት አፈወርቅ ጋር በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ሁኔታዎች ተወያይተዋል።
በዚህም ወቅት፥እያደገ የመጣው የፋሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም የግሉ ዘርፍ ሚና የማይተካ ነው ብለዋል፡፡
የፋሽን ስነ-ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።
በተለይም የማፊ ፋሽን ዲዛይን መሥራች ወ/ሮ ማህሌት አፈወርቅ በመስኩ በትብብር በመስራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል፡፡
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025