አዲስን አበባ፤ መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግንባታ 10 ሚሊዮን ለመሰበሰብ መታቀዱን የከተማ አስተዳደሩ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ገቢው የሚሰበሰበው የግድቡ ግንባታን 14ኛ ዓመት በማስመልከት መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አሰፋ ገልጸዋል።
ለዚህም ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ የመፍጠር፣ የቦንድ ግዢ እና ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል።
የግድቡ ግንባታ ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ የተጀመረውን የቦንድ ግዢ ገቢ ለማሰባሰብ በአስተዳደሩ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የተለያዩ የገቢ ማስገኛ የንቅናቄ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
አቶ ሀብታሙ ሁሉም ዜጋ ለግድቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እና ህዝባዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የድሬዳዋ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው::
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025