ሆሳዕና፤መጋቢት 3/2017(ኢዜአ) ፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡኢ ከተማ አስተዳደር የችፑድ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡
ለሚገነባው የችፑድ ፋብሪካም በዛሬው እለት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የመሰረተ ድንጋይ አኑረዋል፡
በቻይናዊያን ባለሀብቶች በ5 ቢሊዮን ብር ካፒታል የሚለማው "የብሉ ኤሌፋንት ችፑድ ፋብሪካ " ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ተጠናቆ ወደማምረት ስራ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
ፋብሪካው ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ጥራቱን የጠበቁ የችፑድ ምርቶች በማምረት ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፤ ከአንድ ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉና የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025