አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ላይ 27 ባንኮች መሳተፋቸውን ገለፀ።
ባንኮቹ በአማካይ አንድ የአሜሪካን ዶላር ለመግዛት 135 ነጥብ 6185 ብር ማቅረባቸውን ገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ላይ በርካታ ባንኮች መሳተፋቸው መልካም የሚባል መሆኑን አመልክቷል።
በቀጣይ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ባንኩ በነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ የልዩ ውጪ ምንዛሬ ጨረታ ማካሄዱ የሚታወስ ነው።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025