
ቡታጅራ፤ የካቲት 8/2017 (ኢዜአ)፦ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ የሰንበት ገበያዎች እንዲበራከቱ የተደረገው ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የሰንበት የገበያና የንግድ ማዕከላት እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንዳሉት በተለያዩ አካባቢዎች ከ1 ሺህ 213 በላይ የሰንበት ገበያዎች በማቋቋም ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ ተደርጓል።
በዚህም አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የተቀመጠው አቅጣጫ ተጨባጭ ውጤት እያስገኝ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተረጋጋ ገበያን ለመፍጠር እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑም አክለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው በበኩላቸው የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተቀመጡ ሀገራዊ አቅጣጫዎች በመተግበር ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተደራጁ 134 የሰንበት ገበያዎች ከሰንበት እስከ ሰንበት ያለማቋረጥ አገልግሎት እየሰጡና ተጠቃሚ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
አሁን ላይ የሚታየውን የገበያ ዋጋ ውድነትን ለማረጋጋት እያገዘ በመሆኑ መጠናከር አለበት ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የክልልና ከተማ አስተዳደሮች የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025