የኮሪደር ልማት በከተሞቹ የራስ ዐቅም፣ ከሕዝብ ተሳትፎ፣ ከፌደራልና ከልዩ ልዩ ድጋፎች በሚገኝ ዐቅም እየተተገበረ ነው።
በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ እና ወልድያ ከተሞች ተጀምሮ 32.23 ኪ.ሜ መንገድ 27.04 ሄር አረንጓዴና ፓርክ ልማት፣ 3.7 ሄ/ር የሕዝብ አደባባይ፣ 25 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር መብራትና ሕንፃ የማስዋብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
የኮሪደር ልማቱ ከተለመደዉ የፕሮጀክት አፈጻጸም በተለየ ሁኔታ በተለያዩ ምእራፎች ተከፋፍሎ በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እየተተገበረ ነው። ጎንደር፣ ኮምቦልቻና ባሕርዳር ከተሞች የመጀመሪያ ምእራፍ በማገባደድ ወደ ሁለተኛ ምእራፍ ሥራዎች በመሸጋገር ላይ ናቸው፡፡
በዚህ የኮሪደር ልማት እንደ ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ባሉ ከተሞች ግራ እና ቀኝ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገድ፣ ፐብሊክ-ፕላዛ (ማረፊያና መዝናኛ)፣ የመጸዳጃ ቤቶችና ዘመናዊ ካፍቴሪያዎች እየተገነቡ ነው።
በግራ እና ቀኝ ከ5 ሜትር በላይ ስፋት ያለዉ አረንጓዴ ልማት ተከናውኗል። የሐይቅ ዳርቻውን ለሕዝብ የመክፈት ሥራ ተሠርቷል
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025