ባሕር ዳር፤ ጥር 30/2017 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከዘንድሮ የበልግ ወቅት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራስን ለመቻልና ከተረጅነት ለመውጣት የስንዴ መስኖ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትና ሌሎችም የግብርና ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑ ይታወቃል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ባለሙያ ኤልያስ በላይ ለኢዜአ እንዳሉት የበልግ እርሻ እየተከናወነ ያለው በክልሉ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በተለይም በሰሜን ሸዋ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በደቡብና ሰሜን ወሎ ዞኖች እንዲሁም ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
በተያዘው የበልግ ወቅት 239 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በማረስ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ከ168 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን አረጋግጠዋል።
ለበልግ እርሻ በተለያዩ ሰብሎች ከሚለማው መሬት 23 ሺህ 337 ሄክታሩን በስንዴ ሰብል ለመሸፈን የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ለበልጉ የምርት እንቅስቃሴ ማዳበሪያና የምርጥ ዘርን ጨምሮ አጠቃላይ የግብርና ግብአት የማሟላት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በግብርና ልማት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣትና በምግብ ራስን የመቻል ጥረት መሆኑንና ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
በዚህም በዘንደሮው በልግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት ባለሙያው፤ አርሶ አደሮችም ጥሩ ዝግጅት እያደረጉ ነው ብለዋል።
በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት በበልግ ወቅት ከለማው 228 ሺህ 455 ሄክታር መሬት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን የቢሮው መረጃ ያመለክታል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025