🔇Unmute
አምቦ፤ ሚያዝያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ በአምቦ ከተማ በዘጠኝ ወራት ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ወደ ስራ መግባታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በአምቦ ከተማና አካባቢው በተለይም የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን በተመለከተ የከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጂፋራ ጫልችሳ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ከለውጡ በኋላ በዘርፉ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በርካታ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሳተፍ ለብዙ ወገኖች የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በአግሮ እንዱስትሪ፣ በአገልገሎት እና ሌሎችም መስኮች በብዛት እየተሳተፉ መሆኑን አንስተው፤ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራትም ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል።
ከከተማዋ መዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር የመሰረተ ልማትና የመሬት አቅርቦት እንዲሁም ምቹ አገልግሎት እንዲኖር መሰራቱን አስታውሰው በዚህም አልሚዎች እየተበራከቱ መጥተዋል ብለዋል።
በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ 42 ሄክታር መሬት ለአልሚዎች መሰጠቱን ለአብነት ጠቅሰዋል።
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ክልሉ በመሳብ የዜጎችን ተጠቃ...
Apr 23, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ለውጡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰጠው ትኩረት በአስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረ...
Apr 17, 2026
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026