የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አውጥተዋል

May 7, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ኮምቦልቻ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ማውጣታቸውን የፋይዳ ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ገለፁ።

በኮምቦልቻ ከተማ ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አፈጻጸም ያለበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ ተካሄዷል።


ዳይሬክተሩ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

መታወቂያው ለአካታች ኢኮኖሚና የፋይናንስ እድገት፣ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት፣ ህገ-ወጥነትንና ወንጀልን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንኑ ጠቀሜታ በመገንዘብም እንደ ሀገር እስካሁን ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መታወቂያውን ማውጣታቸውን ነው የተናገሩት።

በ2020 ዓ.ም መታወቂያውን 115 ሚሊዮን ለሚደርሱ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ነው ያመለከቱት።

በዛሬው እለት የተካሔደው መድረክ አላማም እስካሁን የነበሩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በክልሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አተገባበር ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል።


መታወቂያው ሀገራዊ መለያ ከመሆኑ ባሻገር የተቀላጠፈ እና ፍትሀዊ አገልግሎትን ለመስጠት፣ ወንጀልን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

መታወቂያውን ከተቋማት ጋር በማስተሳሰርና በማቀናጀት አተገባበሩን ለማሳለጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ በመሆኑም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የፋይዳ መታወቂያ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል።

በቀጣይም ተከታታይ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ሁሉም ዜጎች ፋይዳ መታወቂያን እንዲያወጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አመራሩ በትኩረት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት።


በዞኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች መታወቂያውን ማውጣት ችለዋል ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም ናቸው።

ሁሉም ዜጎች ፋይዳ መታወቂያን እንዲወስዱ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ አመራሩም ህብረተሰቡን በማስተባበር ጭምር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በመድረኩም የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢንዱስትሪ ፓርኩ መገንባት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...

May 20, 2026

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል 

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...

May 7, 2026

የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በማልማት ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማዋል ተግባራት ይጠናከራሉ

ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...

May 7, 2026

ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...

Apr 24, 2026