🔇Unmute
ባሕር ዳር፤ ሚያዝያ 26/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ለቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ዘርፉ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኮሪደር ልማቱ የተጎሳቆሉ ከተሞችን በማልማት ውበታቸው እንዲወጣ አድርጓል።
የከተሞችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸው እንዲነቃቃ ማስቻሉንም ጠቁመዋል።
ከተሞች ለነዋሪዎች የተመቹ እንዲሆኑ ማድረጉን ገልጸው፤ ለቱሪዝም ዘርፉ ማደግና የከተሞችን የኢንቨስትመንት ፍሰት በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አንስተዋል።
በያዝነው ዓመት በ106 ሔክታር ላይ የኮሪደር ልማት ለመሥራት መታቀዱን እና እስካሁን በ80 ሔክታሩ ላይ መከናወኑን አረጋግጠዋል።
በዚህ ሥራም የተሽከርካሪና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ 108 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልማት መከናወኑን አስታውቀዋል።
በተሠራው የኮሪደር ልማት 10 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ 168 ደረጃቸውን የጠበቁ ካፍቴሪያዎች፣ የሕጻናት መዝናኛዎች፣ የአረጋውያን ማረፊያዎችና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ስፍራዎች መካተታቸውን አብራርተዋል።
ለኮሪደር ልማቱ ከ6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮኑ ሕብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበቱና ቁሳቁስ ተሳትፎ ያደረገበት መሆኑን አስገንዝበዋል።
በኮሪደር ልማቱ ለ112 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም አመላክተዋል።
በቀጣይ ልማቱን ወደ ሌሎች ከተሞች የማስፋቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያመላከቱት።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026