የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኩነቶች ምዝገባ ሥርዓትን በማጠናከር የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል 

Apr 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሚያዚያ 21/2018(ኢዜአ)፦ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኩነቶች ምዝገባ ሥርዓትን በመተግበር የተገልጋዩን እርካታ የማሳደግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአማራ ክልል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ።

‎የክልሉ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ‎ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያለማውን የኩነቶች መመዝገቢያ ሲስተም ዛሬ ተረክቧል።

‎‎የአገልግሎቱ ኃላፊ ወይዘሪት መዓዛ በዛብህ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መጠቀም አስፈላጊ ነው።

‎‎ለዚህም ተቋሙ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለምቶ ዛሬ የተረከበው የኩነት መመዝገቢያ ሲስተም መሰረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል።

‎‎አሁን ላይ የለማው የኩነት መመዝገቢያ ሲስተም የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂው ስራውን ከማቀላጠፍ ባሻገር ጥራት ያለው መረጃን ለተጠቃሚው ማህብረሰብ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዘው አስረድተዋል።

ይህም በክልሉ በተመረጡ 477 የምዝገባ ጣቢያዎች ሲስተሙ ቀደም ብሎ ተግባራዊ ተደርጎ ሲፈተሽ መቆየቱንም አመልክተዋል።

‎በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለትራንስፖርት፣ ለወረቀት፣ ለህትመትና ሌሎች ወጪዎች ይወጣ የነበረን 11 ሚሊዮን ብር ማዳን ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይም አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈውን የኩነቶች ምዝገባ ስርአትን በማጠናከር የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግ ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ አንስተዋል።

‎‎የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በምርምርና ሌሎች ተግባራት ተወዳዳሪነትቱን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ለዚህም የክልሉን ተቋማት ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ከክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

‎‎እስካሁንም ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የመንግስት ተቋማት ሲስተም በማልማትና በመዘርጋት ሥራቸውን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ሥራ መስራቱን ተናግረዋል።

‎‎የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ በዩኒቨርሲቲው የለማው የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ሲስተም በዕቅድ ላይ የተመሰረተ ክልላዊ ልማት ለማካሄድና ፖሊሲና ስትራቴጂን ለማውጣት ያግዛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢንዱስትሪ ፓርኩ መገንባት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...

May 20, 2026

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል 

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...

May 7, 2026

የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በማልማት ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማዋል ተግባራት ይጠናከራሉ

ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...

May 7, 2026

ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...

Apr 24, 2026