🔇Unmute
አርባ ምንጭ፤ሚያዚያ 8/2018 (ኢዜአ)፡-በአርባ ምንጭ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጣቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) በከተማው በለውጡ ዓመታት ከ400 በላይ የልማት ፕሮጀክቶች መከናወናቸውንና ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በሰው ተኮር እሳቤ የተቃኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና የልማት ፕሮጀክቶች ሁሉንም ነዋሪዎች ያማከሉ ሲሆን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲረጋገጥ ያስቻሉ መሆኑን ተናግረዋል።
አርባ ምንጭ ከተማ ሰፊ ፀጋ ያላት ብትሆንም ቀደም ባሉ ጊዜያት የሚፈለገው ዕድገት እንዳልተመዘገበ ጠቅሰው የለውጡ መንግስት በተከተለው አዲስ እይታ የከተማዋ ዕድገት እየተፋጠነ ይገኛል ብለዋል።
ከጤና ልማት አኳያ በለውጡ ዓመታት ሦስት ሆስፒታሎችንና ሁለት ጤና ጣቢያዎችን ገንብቶ በባለሙያና በቁሳቁስ በማሟላት ነዋሪው ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።
በትምህርት ዘርፍም ትምህርት ቤቶችን በቤተመጻሕፍትና በቤተሙከራ በማደራጀት እንዲሁም አዳሪ ትምህርት ቤት በመገንባትና ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ተሰርቷል ብለዋል።
በሰው ተኮር ማህበራዊ ልማትም ለበርካታ አረጋዊያንና አቅመ ደካማ ወገኖች ቤት የመገንባትና የማደስ ሥራ በማከናወን እንዲሁም በምገባ አገልግሎት ተስፋቸውን ለማለምለም መቻሉን ነው የገለጹት።
ከመንገድ መሠረተ ልማት አኳያም የተለያዩ አካባቢዎችን የሚያገናኝ የአስፋልት፣ የድንጋይ ንጣፍና የጠጠር መንገድ ሥራዎችን በማከናወን የህዝቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ ተደርጓል ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ የተጀመረው የገበታ ለትውልድ፣ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች አርባ ምንጭ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ አቶ አታሼ አብሬ በበኩላቸው፣ ከተማዋ በተፈጥሮ የተቸራት በርካታ ፀጋዎች ቢኖሯትም ለዘመናት ዕድገቷ በሚፈለገው ደረጃ ላይ ሳይፋጠን መቆየቱን ገልጸዋል።
ነገር ግን ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከናወኑ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ከማሳደግ ባለፈ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በተለይ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የገለጹት።
የተለያዩ የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ካልተፈለገ ወጪ እና እንግልት ታድጎናል ነው ያሉት።

የከተማዋን ልማት ከዚህም በላይ ለማፋጠን ከመንግስት ባለፈ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል።
በአካባቢያችን ሪፈራል ሆስፒታል መገንባቱ ለሕክምና ወደተለያየ አካባቢ ስንሄድ እናወጣው የነበረውን ተጨማሪ ወጪ አስቀርቶልናል ያሉት ደግሞ አቶ ብርሃኑ ከበደ ናቸው።

እየተገነባ ያለው የአርባ ምንጭ ስታዲየም የስፖርት ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ ለከተማው ልዩ ድምቀት እንደሚሆንም አመልክተዋል።
አርባ ምንጭ በርካታ የተፈጥሮ ፀጋ ያላት ከተማ እንደመሆኗ ከተማዋን ከአባያ እና ጫሞ ሐይቆች እንዲሁም ከተለያዩ የመስህብ ስፍራዎች ጋር አስተሳስሮ የማልማቱ ሥራ መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026