የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ለበዓል የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር የተቀናጀ ቁጥጥር እየተደረገ ነው

Apr 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦ለትንሳኤ በዓል የምርት አቅርቦትና የገበያ አማራጮችን በማስፋት የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር የተቀናጀ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም በተለያዩ አካባቢዎች በርከት ያሉ ጊዜያዊ የገበያ ስፍራዎች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው ታውቋል።


የበዓል ገበያ አቅርቦት፣ ቁጥጥርና አጠቃላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ኢዜአ የደሴ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ዮናስ እንዳለ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ኃላፊውም በማብራሪያቸው በከተማዋ እና አካባቢው የተለያዩ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የእርድ እንስሳት በብዛት እየቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶችን ጭምር በብዛትና በጥራት ለማቅረብ ቀደም ተብሎ ዝግጅት መደረጉን አንስተው በዚህም መሰረት የምርት አቅርቦትና የገበያ አማራጮችን በማስፋት የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በግብይት ወቅት ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ነጋደዎች ሲያጋጥሙም ህብረተሰቡ ለሚመለከታቸው አካላት ወይንም የጸጥታ አካላት መረጃ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል።


ለበዓል ሲገበያዩ ካገኘናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ መሰረት ተስፋዬ እና አቶ ዳዊት አራጌ፤ ለበዓል የምርት አቅርቦትና ተደራሽነቱ መልካም ቢሆንም በተለይም በሸቀጦች ላይ መጠነኛ ጭማሬ ስለመኖሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም በተቋቋሙት ጊዜያዊ የገበያ ማእከላት ምርቶችን በተሻለ ዋጋ በማግኘታቸው መሸመታቸውን ተናግረዋል።


በተጨማሪም ዘይት፣ ስኳር፣ የዳቦ ዱቄትና ሌሎች የኢንዱስትሪ ውጤት የሆኑ ምርቶችም በሸማቾች ህብረት ስራ ማህብራት በኩል መቅረባቸውን ገልጸዋል።

ለበአል በየአካባቢው ጊዜያዊ የገበያ ማእከላት መቋቋማቸው በአማራጭነት ከመግዛት ባለፈ በቅርበት መሸመት የሚያስችሉ በመሆናቸው መልካም ጅምር መሆኑን ሸማቾቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢንዱስትሪ ፓርኩ መገንባት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...

May 20, 2026

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል 

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...

May 7, 2026

የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በማልማት ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማዋል ተግባራት ይጠናከራሉ

ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...

May 7, 2026

ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...

Apr 24, 2026