
ጎንደር፤ መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፡- ዩኒየኖችና የህብረት ስራ ማህበራት ለአርሶ አደሩ የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሻሻል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የማእከላዊ ጎንደር ዞን ህብረት ስራ ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጸሀይ ሁለገብ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን 25ኛ ዓመት ምስረታ በአል አከባበርና 23ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ተስፋሁን ተሰማ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት ዩኒየኖችና የህብረት ስራ ማህበራትን በመደገፍና በማበረታታት የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
በዚህ ዓመትም ለጸሃይ ዩኒየን ብቻ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር እንዲያገኝ በማድረግ ማዳበሪያና ሌሎች ግብአትና ምርቶችን በወቅቱ እንዲያቀርብ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል።

የጸሀይ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይሁኔ ዳኘው በበኩላቸው ለ2017/18 ምርት ዘመን መኽር ወቅት እርሻ የሚውል ከ600 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እየተሰራ ነው።
እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ ከ165ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በማስገባት ከ75 ሺህ ኩንታል በላይ የሚሆነው ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን አስረድተዋል።
በተጨማሪም በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ 71 ሺህ ኩንታል የግብርና ምርቶችን ከአርሶ አደሩ በመረከብ ገበያ የማረጋጋት ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒየኑ ባቋቋመው የምግብ ዘይት ፋብሪካ 71 ሺህ ኩንታል የቅባት እህል በመረከብ 180ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በአምስት ትራክተሮች፣ በሁለት መውቂያ ማሽኖችና በሁለት የጸረ ተባይ መርጫ መሳሪያዎች በመታገዝ ለአርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም አመልክተዋል።
ዩኒየኑ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል የግብርና ምርቶቹን ገበያ አፈላልጎ በተሻለ ዋጋ በመሸጥና የኢንዱስትሪ የፍጆታ ምርቶችንም በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።

የዩኒየኑ አባል አርሶ አደር አስፋው ጥላሁን በበኩላቸው ዩኒየኑ ለመኸር እርሻ የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እያቀረበ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አርሶ አደር ካሳው በቀለ በበኩላቸው ዩኒየኑ የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብ ለከተማው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።
ጸሃይ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ከ145 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉትና ካፒታሉም 78 ሚሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026