
ይርጋለም፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):- ይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤክስፖርትና ተኪ ምርቶችን በማምረት በአገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በፓርኩ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አራት ባለሀብቶችን ስራ የማስጀመርና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን የማስመረቅ መርሃግብር ዛሬ ተከናውኗል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሀመድ እንዳሉት የተቀናጁ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ፣ ወጪ ምርትን በማሳደግና ከውጭ የሚገቡትን በመተካት ሚናቸው ጉልህ ነው፡፡
ፓርኮቹ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን መዋቅራዊ ሽግግር በማጠናከር ለአገር ኢኮኖሚ ግንባታ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱም ገልጸዋል፡፡
ከእነዚህ አንዱ የሆነው ይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ኢንዱስትሪ ፓርክ የወጪና ተኪ ምርቶችን በማምረት በአገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የይርጋለም የተቀናጀ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቦርድ ሰብሳቢና የሲዳማ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ አራርሶ ገረመው(ዶ/ር) በበኩላቸው በፓርኩ ስራ የጀመሩ ፋብሪካዎች ተገቢውን ግብዓት እንዲያገኙ ምርታማነትን የማሳደጉ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በፓርኩ የዛሬዎቹን ጨምሮ ስምንት ባለሃብቶች በአቡካዶ ዘይት፣ በወተት፣ በማርና ቡና ምርት የማቀነባበር ስራ እያከናወኑ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃይሉ የተራ ናቸው፡፡
ዛሬ ወደ ስራ የገቡት አራት ባለሃብቶች ከአንድ ቢለዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው አንድ ሺህ ለሚጠጉ ዜጎችም ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ፓርኩ ባለፉት አምስት ዓመታት ከ23ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረና ምርታማነቱ እያደገ በመሆኑ የግብዓት፣የመሰረተ ልማትና የግብይት ስርዓቱን ለማሳለጥ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
አዳዲስ ፋብሪካዎቹን ስራ ከማስጀመር በተጨማሪ በቀን 200 ሜትሪ ኪዩብ ፈሳሽ ቆሻሻ የሚያጣራ ፕላንት፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማእከልና የህጻናት ማቆያም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026