
ቦንጋ፤የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፦የቦንጋ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርተፍኬሽን ማዕከል በስምንት ወራት 53 ሺህ 14 ቶን ደረቅና የታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የቦንጋ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርተፍኬሽን ማዕከል ከተቋቋመ ስምንት ወራት አስቆጥሯል።
ማእከሉ ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁንም ደረቅና የታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በብዛትና በጥራት በማቅረብ ላይ ይገኛል።
የማእከሉን የስራ እንቅስቃሴ በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የማዕከሉ ኃላፊ አቶ ያሲን አባጊሶ፤ የማዕከሉ አገልግሎት በተለይም ለቡና ነጋዴዎችና ኤክስፖርተሮች የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም የቦንጋ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርተፍኬሽን ማዕከል በስምንት ወራት ብቻ 53 ሺህ 14 ቶን ደረቅና የታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን ገልጸዋል።
ከካፋ ዞን በተጨማሪ ከሸካና ቤንች ሸኮ አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፥ ቡናው ተመርምሮ ደረጃ ከወጣለት በኋላ በቀጥታ ውል መሠረት ግብይት እንደሚፈፀምም ተናግረዋል።
የነጋዴዎች እና ኤክስፖርተሮች ወኪል አቶ ሰይድ ሳኒሀሰን፤ የቦንጋ ማዕከል ከተከፈተ በኋላ የነበረው እንግልትና ያልተገባ ወጪ መቅረቱን አንስተዋል።
ሌላው የቡና አቅራቢዎች እና ኤክስፖርተሮች ወኪል አቶ ወንድዬ ምትኩ፤ ከዚህ ቀደም በጅማ ማዕከል ላይ በነበረው ጫና መኪኖች ቡና ጭነው ለበርካታ ቀናት ስለሚቆዩ ከፍተኛ ችግር እንደነበር አስታውሰው፥ የማእከሉ መከፈት እነዚህን ሁሉ ችግሮች አስቀርቷል ብለዋል።
የቦንጋ ማዕከል ስራ በመጀመሩ የቡና ምርት በአጭር ጊዜ ውስጥ ደረጃ ወጥቶለት ለገበያ ማቅረብ አስችሏል ተብሏል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026