የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በዞኑ በበጋ መስኖ ተመርተው ለገበያ የቀረቡ ምርቶች ገበያን ማረጋጋት ችለዋል

Apr 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በበጋ የመስኖ ልማት ተመርቶ ለገበያ የቀረበ ከ4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ገበያውን በማረጋጋት አስተዋጽኦ ማበርከቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ።

በመምሪያው የመስኖ ልማት ቡድን መሪ ሀውልቱ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በዞኑ በበጋው ወራቶች ሁሉንም የውሃ አማራጮች በመጠቀም ከ48 ሺህ ሔክታር በላይ በመስኖ ማልማት ተችሏል፡፡


ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ15 ሺህ ሔክታር፤ የተገኘው ምርትም በ1 ሚሊየን ኩንታል ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ ገበያን መሰረት አድርጎ እንዲሠራ በተደረገለት ድጋፍና ክትትል መሰረትም፤ ጤፍ፣ ሩዝ፣ በቆሎ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ድንችና ጥቅል ጎመን በማምረት ለገበያ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።

በአይነትም ሆነ በብዛት ተመርቶ ለገበያ የቀረበው ምርት የገበያ ዋጋን ከማረጋጋቱ ባለፈ፤ ሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን እንዲያገኝ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

አርሶ አደሩ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በስፋት በመጠቀም ለዘመናዊ የመስኖ ልማት መስፋፋት ትኩረት መስጠቱንም ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ለመስኖ አልሚ አርሶ አደሮች ከ4 ሺህ በላይ የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን ጨምሮ ከ50 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በማቅረብ ለመስኖ ልማቱ ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

በዞኑ የተገነቡ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የመስኖ አውታሮችም አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት ተላቆ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበትን እድል ፈጥረዋል ነው ያሉት።


አንደኛው ዙር የመስኖ ልማት ተጠናቆ ሁለተኛው ዙር መጀመሩን ጠቁመው በአሁኑ ወቅትም፤ ከ10 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በመስኖ እየለማ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው

ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...

May 15, 2026

በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ ነው -ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ

ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...

Apr 22, 2026

ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለአፍሪካ አገራት ትልቅ አርአያ ናቸው - የላይቤሪያ ልዑካን ቡድን

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...

Apr 16, 2026

ሀገራዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...

Apr 3, 2026