🔇Unmute
ሆሳዕና፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ በተደረገ ጥረት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ18 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መቻሉም ተመላክቷል።
የቢሮው ኃላፊ ቀመሪያ ረሻድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ በህዝብ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ያስፈልጋል።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አመልክተዋል።
በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ በተደረገ ጥረት ከ18 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
እንደ ኃላፊዋ ገለጻ በዘጠኝ ወራት የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡
ስኬታማ የግብር አሰባሰብ ሥራ ለማከናወንም ዘመናዊ የታክስ አሰባሰብ ስርዓትን ከመዘርጋት ባለፈ በግብር ሕጉ ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥና የታክስ ህግን የማስከበር ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሁሉንም የገቢ አማራጮች በአግባቡ ለመጠቀም ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
በቀሪ ወራትም በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ክልሉ ያለውን የገቢ አማራጭ በአግባቡ ለመጠቀም በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በሆሳዕና ከተማ የአጋፔ ሆቴልና ሪስቶራንት ባለቤት አቶ መላኩ መኮንን በበኩላቸው ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል ለአካባቢ ልማት መፋጠን ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ገልጸው፣ በተሰማሩበት የንግድ ሥራ ግብራቸውን በመክፈል ለአካባቢው ልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ በመክፈል ለሀገር እድገትና ለዜጎች ተጠቃሚነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉም ነው የገለጹት።

ግብርን በወቅቱ መክፈል ልማት በማፋጠን የህዝብን የልማት ፍላጎት ለማሟላት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በሆሳዕና ከተማ የአቢሲኒያ የወንዶች ልብስ ስፌት ድርጅት ባለቤት አቶ ብርሃኑ አያሌው ናቸው፡፡
የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ እንደሆኑ የገለጹት አቶ ብርሃኑ በየዓመቱ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንደሚከፍሉ ተናግረዋል፡፡
ግብር ለራስ ልማት እንደሚውል በመገንዘብ ያለማንም ቀስቃሽ ግብርን በወቅቱ የመክፈል ግዴታን መወጣት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026