🔇Unmute
ቢሾፍቱ፤ ሚያዚያ 7 /2018 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ግልጽ ዕቅድ በማስቀመጥ የሕዝቡን ሕይወት የሚቀይሩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የፓርቲ የሦስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱራህማን፣ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፤ ባለፉት ዓመታት የክልሉ መንግስት ግልጽ ዕቅድ በማስቀመጥ የሕዝቡን ሕይወት የሚቀይሩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል።
በተለይም በሁሉም ዘርፎች በኢኒሼቲቭ መልክ ሲተገበሩ የቆዩ የልማት ስራዎች በክልሉ መሰረታዊ ለውጦች እንዲመዘገቡ ያስቻሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

በመድረኩ ላይ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የመንግስት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው፣ የታዩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ተለይተው ለቀጣይ ሥራዎች አቅጣጫ ይቀመጣልም ተብሏል።
በተጨማሪም የ2019 ዓ.ም የዕቅድ መነሻ የሚቀርብ ሲሆን፣ በግምገማው ላይ የዞን፣ የከተማ እና የወረዳ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026