የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጠንካራ የዕድገት አፈጻጸም አስመዝግቧል    

Apr 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጠንካራ የዕድገት አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማስቻሉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለጹ።

የገንዘብ ሚኒስቴር በ18 ወራት የተከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ውጤታማነት የሚገመግም ዝርዝር ሪፖርት ይፋ አድርጓል።


ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ ተግባራዊ የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመዘገቡ እያደረገ ይገኛል።

የሀገሪቱ አጠቃላይ ምርት ተከታታይነት ያለው ዕድገት እያሳየ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አስችሏታል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፉ የኢኮኖሚው ሞተር ሆኖ መቀጠሉን ጠቅሰው፤ የግብርና እና የአገልግሎት ዘርፎች የላቀ አፈጻጸም እያሳዩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃው ካመጣቸው ትልቁ ድሎች አንዱ ላለፉት ዓመታት ፈታኝ ሆኖ የቆየውን የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉ መሆኑን ገልጸዋል።

የተቀናጀ የፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲ ተግባራዊ መደረጉ የኑሮ ውድነቱን ጫና በማቃለል ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገቡን አብራርተዋል።

የምንዛሬ ተመን ማሻሻያውን ተከትሎ በሀገሪቱ የወጪ ንግድ ላይ ታሪካዊ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል።


የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም ገበያ ያላቸው ተወዳዳሪነት በመጨመሩና ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ ማደጉን ጠቅሰው፤ ከዚህ በተጨማሪ የሐዋላ ገቢ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትና የውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ የታየው መሻሻል ከፍተኛ ነው ብለዋል።

መንግሥት የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማዘመኑ ጠቅላላ ገቢው ከፍ እንዲል ማድረጉን ጠቅሰው፤ ይህም የሀገሪቱን የውጭ ዕዳ ጫና በዘላቂነት ለመቀነስ እየተደረገ ያለውን ጥረት በእጅጉ ማገዙን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተቀናጀ አመራርና በማስረጃ ላይ በተደገፈ ትንታኔ እየተመራ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም መዋቅራዊ ለውጦችን በማጠናከር የተረጋጋና እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...

May 15, 2026

ረቂቅ አዋጁ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...

Apr 23, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ በኢኮኖሚው መስክ ትብብራቸውን ያጠናክራሉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...

Apr 17, 2026

በጀጎል ግንብ ውስጥ የሚገነባው የ”ዳር ሀረር” የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...

Apr 12, 2026