አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/ 2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ዓላማን በመደገፍ ለትግበራው ያሳየችው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ሲሉ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሴክሬተሪያት የማስተባበሪያና ፕሮግራም ዳይሬክተር ሶቴሲ ማኮንግ(ዶ/ር) ገለጹ።
ዳይሬክተሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ነጻ የንግድ ቀጣና የአህጉሪቷን የንግድ ልውውጥ ለማጠናከር እና ለስራ እድል ፈጠራ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
በንግድ ቀጣናው በሚደረግ የንግድ ልውውጥ በትራንስፖርት፣ ንግድ፣ አገልግሎትና ሌሎች ዘርፎች የሚኖረው ሰንሰለት ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናውን ዓላማ በመደገፍ ለትግበራው ያሳየችው ቁርጠኝነትና እያደረገች ያለው ዝግጅት የሚደነቅ እንደሆነ ተናግረዋል።
ነጻ የንግድ ቀጣናው ያመጣውን ዕድል ለመጠቀም ነጋዴዎችና ኢንቨስተሮች ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
የአፍሪካ አገራት በአህጉሪቱ ያለውን የንግድ ልውውጥ ከቀረጥ ነጻ ለማድረግ ያደረጉት ስምምነት ለነጋዴዎችና አምራቾች ምርትን ለማሳደግና ንግድን ለማስፋት ትልቅ ዕድል ይዞ መምጣቱን ነው የገለጹት።
እ.ኤ.አ በ2050 ከአፍሪካ ህዝብ ቁጥር ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ወጣት እንደሚሆን መተንበዩን በማስታወስ የስራ እድል ፈጠራ እድሎችን ማስፋት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው እንደሆነም ነው የተናገሩት።
በዚህ ረገድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና በስራ እድል ፈጠራ ያለውን እድል አሟጦ ለመጠቀም ከወዲሁ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሴክሬተሪያት ትግበራውን ለማሳለጥ ሃገራትን በማስተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025