አርባ ምንጭ፣ ሐምሌ 16/2017(ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን በሀገር በቀል ምርቶች የመጠቀምና በራስ ምርት የመኩራት ባህልን ለማዳበር ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
"የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ሀሳብ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጋራ በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ያዘጋጁት የንግድ ባዛርና አውደ ርዕይ እየተካሄደ ነው።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን በክልሉ ከውጭ የሚገቡትን የሚተኩ ምርቶች እየተመረቱ መሆኑን ገልጸው፣ ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ አቅም እንዳለ ጠቁመው፣ ተኪ ምርቶችን በስፋትና በጥራት የማምረቱ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የህብረተሰቡን ሀገር በቀል ምርቶች የመጠቀም እና በራስ ምርት የመኩራት ባህልን ለማዳበር ግንዛቤን ከማሳደግ ጎን ለጎን ምርቶችን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ያለው ባዛርና አውደ ርዕይ ህብረተሰቡ የሀገር ምርትን እንዲጠቀም ዕድል ከመስጠት ባለፈ ለአምራቾችና ነጋዴዎች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለውም ወይዘሮ ሰናይት ተናግረዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ጥራትን መሰረት ያደረገ የምርት ሂደት በመከተልና ፈጠራንና እሴትን በመጨመር የኤክስፖርት ምርትን ተፈላጊነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል።
የንግድ ባዛርና አውደ ርዕዩ ተሳታፊዎችም የሀገር ምርት የመጠቀም ባህልን ማዳበር ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ገልፀዋል።
የሀዋሳ ጋርሜንት ሽያጭ ባለሙያ ወይዘሪት ሄዋን ወልደጊዮርጊስ ድርጅቱ የውጭ ምርቶችን የሚተኩ የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶችን በማምረት ለገበያ እያቀረበ መሆኑን ገልጻለች።
"በባህል ወረራና ዘመናዊነት ጫና ውስጥ በመውደቃችን ለሀገር ምርት ትኩረት ሳንሰጥ ቆይተናል" ያለቸው ባለሙያዋ፣ በእዚህም በሀገር ውስጥ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶች እያሉ የውጭ ምርቶች የጥራት ደረጃቸውን ሳናረጋገጥ እንጠቀማለን ብላለች።
ሁሌም በሀገር ምርት መኩራት እንደሚገባ ገልጻ፣ በሀገር ምርት መጠቀም አምራቹን ከማበረታታት በተጨማሪ ለሀገር ኢኮኖሚ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጻለች።
በየጊዜው የሚዘጋጁ የንግድ ባዛርና አውደርዕዮች ዜጎች የሀገር ምርት የመጠቀም ልማዳቸው እያደገ እንዲመጣ ያግዛል ያሉት ደግሞ የአቢሲንያ ቆዳ ውጤቶች አቅራቢ ድርጅት ባለቤት አቶ አበበ ዲታ ናቸው።
ድርጅቱ በባዛርና አውደርዩ ላይ የተለያዩ የቆዳ ጫማዎች፣ ዋሌቶች፣ ቀበቶዎች እና ቦርሳዎችን ይዞ መቅረቡን ገልጸው፣ ይህም የሀገር ምርትን ከማስተዋወቅ ባለፈ የገበያ ትስስር በመፍጠር ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል።
ዜጎች የሀገራቸውን ምርት እንዲጠቀሙና በሀገር ምርት እንዲኮሩ የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫና ምርትን የማስተዋወቅ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
ለሁለት ሳምንት በሚቆየው ባዛርና አውደ ርዕይ ከ150 በላይ ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን በማቅረብ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025