አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2017(ኢዜአ)፦የኮሪደር ልማቱ ከተጎሳቆለ አካባቢ በማላቀቅ የተሻለ ህይወት ለመምራት እንዳስቻላቸው የመዲናዋ የመልሶ ማልማት ተነሺዎች ገለጹ።
አዲስ አበባ ከለውጡ ወዲህ ስሟን እና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የሚመጥን ገጽታ ለማላበስ እና የነዋሪዎቿን ህይወት ለማሻሻል በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በዚህም የሚታዩ ለውጦች ተመዝግበዋል።
በዚህም መዲናዋ ውብ፣ ጽዱ እና የዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የስህበት ማዕከል እየሆነች መጥታለች፡፡
በተለይ በሁለት ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተከናወነው እና በመከናወን ላይ ያለው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ገጽታ እና ለነዋሪዎች ህይወት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
ኢዜአ በኮሪደር ልማቱ ከከተማዋ የተለያዩ ሰፈሮች ተነስተው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አዲስ እና ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ አካባቢ ህይወት መምራት የጀመሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋግሯል።
ከፒያሳ በመልሶ ማልማት የተነሱት አልማዝ ዳምጠው፤ ቀደም ሲል በተጎሳቆለና ለህይወት ፈታኝ በሆነ አኗኗር ውስጥ ያሳልፉ እንደነበር አውስተዋል።
የኮሪደር ልማቱ መምጣቱን ተከትሎ መኖሪያ አካባቢያቸው ወደ መልሶ ማልማት ሲገባ፥ እነሱም ምቹ ካልሆነው አሮጌ አካባቢ ወጥተው ደረጃውን ወደጠበቀ የመኖሪያ መንደር መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ልማቱ ከነበርንበት ደሳሳ ጎጆ በመውጣት በተሻለ ሁኔታ እንድንኖርና ልጆቻችን በምቹ ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡
ከቄራ በመልሶ ማልማት የተነሱት ሙና ሸሪፍ በበኩላቸው፤ አሁን ያሉበት አካባቢ በውሃ፣ በጤና፣ በመብራትና ሌሎች አቅርቦቶች ከበፊቱ እጅግ የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ የስፖርት ማዘውተሪያ ያላቸው፣ የመመገቢያ ማዕከል የተገነባላቸው እና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟሉ በመሆናቸው መንግስትን እናመሰግናለን ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ሰናይት ገብሩ ናቸው፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025