አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ማሻሻያ ዳያስፖራውን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአሰራር ማሻሻያ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለኢዜአ እንዳሉት የዳያስፖራ ፖሊሲ ስራ ላይ ከዋለ አስራ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል።
በእነዚህ አመታትም በምጣኔ ሃብት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች በተደረጉ ማሻሻያዎች በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
በተለይም ባለፉት ሰባት አመታት በውጭና በአገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርግ ምጣኔ ሃብት ለመገንባት የተለያዩ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን አንስተዋል።
በአሁኑ ወቅትም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ የሚሆኑበት የአሰራር ማሻሻያ በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በቅርቡ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ሁለተኛው የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት መርሃ ግብርን ታሳቢ ያደረገ ማሻሻያ ማስፈለጉን በማንሳት።
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያም በተለያየ የአለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ የሚሆኑበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ካሉበት ሆነው ገንዘባቸውን በሚፈልጉበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ ማዋል የሚያስችል አሰራር በመሆኑ ፖሊሲው በዚሁ አግባብ የተቃኘ እንደሆነ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት አንዷ በመሆኗ በዚህ ወቅት የሚደረግ ኢንቨስትመንት አዋጭ እንደሆነም አምባሳደር ፍጹም ተናግረዋል።
በመሆኑም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እድሉን በመጠቀም የኢንቨስትመንት ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዲያስፖራው አገሩንና እራሱን ተጠቃሚ እንዲያደርግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም አምባሳደር ፍጹም አረጋ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025