የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የበለጠ በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

Jul 21, 2025

IDOPRESS

አሶሳ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የበለጠ በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን አስገነዘቡ።

የክልሉ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እየተገመገመ ነው።

በመድረኩ አቶ አሻድሊ ሀሰን እንደተናገሩ፤ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ በኩል አበረታች ውጤቶች የታዩበት ነው።


በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ ሥራዎችን እስከታች በማውረድ ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

‎በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የሕዝቡን ጥያቄ የመለሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ይህም የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል ነው ያሉት።

‎በግብርና እና በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የተከናወኑ ተግባራትም ህዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ አቅርቦትን በማሻሻል ገበያ ማረጋጋት መቻሉን አንስተዋል።


በማዕድን ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን እንደ አብነት ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአጠቃላይ በክልሉ የተከናወኑ አበረታች ተግባራትን በላቀ ጥረት በማስቀጠል በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

‎አመራሩ በተቀናጀ ሁኔታ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

እስከ ነገ በሚቆየው መድረክ የ2017 በጀት ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ግምገማና ውይይት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.