አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሀገሮች በልማት በሚተሳሰሩባቸው ምቹ ሁኔታዎች ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለፁ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሲካሔድ የቆየው የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም የማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።
አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሀገሮች በልማት በሚተሳሰሩባቸው ምቹ ሁኔታዎች ላይ በትኩረት እየሰራች ትገኛለች።
በተለይም የአህጉሪቱ ወጣቶች በልማት፣ በኢኮኖሚና በስራ እድል ፈጠራ የሚቀናጁበትን ሁኔታ ማመቻቸት አንዱና ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል።
ላለፉት ሦስት ቀናት የተካሔደው የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም የዚሁ አካል መሆኑንም ገልጸው በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ሀገሮች በኢኮኖሚ፣ በልማትና መሰል ተግባራት ላይ ያላቸው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን አንስተዋል።
ይህም የአህጉሪቱን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት ጥቅም ላይ ለማዋል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በለውጡ ዓመታት ያካሄደችው ሀገራዊ ሪፎርም እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን ወጥ በሆነ መልኩ ማከናወን እንዳስቻላት አስታውቀዋል።
በተለይም አምስት የኢኮኖሚ ልማት ምሰሶዎችን በመለየት እያከናወነች ባለው ተግባር አበረታች ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል።
የአህጉሪቱን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ አካታች የኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆኑንም ነው አቶ አደም ፋራህ የጠቆሙት።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025