ነቀምቴ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦በምስራቅ ወለጋ ዞን በሰፈነው ሰላም የልማት ሥራዎችን በፍጥነትና በጥራት ለማከናወን መቻሉን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ወጋሪ ነገራ ገለጹ።
በዞኑ ሲቡ ስሬ ወረዳ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርገው የተገነቡ 41 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ወጋሪ ነገራ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በዞኑ የሰፈነው ሰላም የልማት ሥራዎችን በስፋት ለማከናወን እድል ፈጥሯል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት እየበቁ መሆኑን ገልጸዋል።
በዞኑ ሲቡ ሲሬ ወረዳ በ435 ሚሊዮን ብር የተገነቡ 41 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችም የዚሁ ጥረት አካል መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለአገልግሎት እየበቁ ያሉ የመሰረተ ልማት ተቋማት የትምህርት፣ የጤና፣ መሰረተ ልማት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን የሚያሳድጉ ናቸው ብለዋል።
በዞኑ ሁሉንም ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች እንደሚጠናከሩ ገልጸው፣ የዞኑ ህዝብም የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
የሲቡ ስሬ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ጨነቀ ቡሻ በበኩላቸው ለአገልግሎት የበቁ የመሰረተ ልማት ተቋማት በመንግሥት በጀትና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ ናቸው ብለዋል።
የፕሮጀክቶቹ ለአገልግሎት መብቃት ለዓመታት ሲነሱ ለነበሩ የህብረተሰብ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም የወረዳውን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ሥራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል።
በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ ምርቃት ላይ የተገኙት የወረዳው ነዋሪዎችም የልማት ሥራው ተጠቃሚነታቸውን የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025