ጋምቤላ፤ ሰኔ 30/2017(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በበጀት ዓመቱ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 223 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
በግብርናው ዘርፍ ፍቃድ የወሰዱ 38 ባለሃብቶች በሙሉ የእርሻ መሬት ተረክበው ወደ ስራ መግባታቸውም ተገልጿል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለፁት በክልሉ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ በተሰሩ ስራዎችና በአካባቢው የሰፈነው ሰላም የአልሚ ባለሃብቶች ፍሰት እንዲጨምር አስችሏል።
በዚህም በ2017 በጀት ዓመት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 223 ባለሃብቶች ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
ባለሃብቶቹ ፈቃዱን የወሰዱት በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት መሆኑንም ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል 123ቱ መሬት ተረክበው ወደ ልማት መግባታቸውንም ገልፀዋል።
ፍቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ከ11ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
በግብርናው ዘርፍ ብቻ ፈቃድ ከወሰዱ ባለሃብቶች 38ቱ የእርሻ መሬት ተረክበው ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ጋምቤላ ወረዳ በግብርና ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ባለሀብቶች መካከል አቶ ኡሞድ ኡገር በሰጡት አስተያየት ለግብርና ልማት የተረከቡትን የእርሻ መሬት ማልማታቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሚያደርግላቸው ክትትልና ሙያዊ እገዛ በስራችው ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዙን ጠቁመዋል።
በክልሉ ለግብርናው ኢንቨስትመንት ዘርፍ ምቹና ተስማሚ ስነ-ምህዳር በመኖሩ የተረከቡትን የእርሻ መሬት ማልማታቸውን የገለጹት ደግሞ በክልሉ አቦቦ ወረዳ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ ፍቅሬ ገብረ መድህን ናቸው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025