የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በጉጂ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጡ ይገኛሉ

Jul 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2017(ኢዜአ)፦በጉጂ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጡ እንደሚገኙ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ከፍያለው ተፈራ ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ቡድን በሶስተኛ ቀን ውሎው በጉጂ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም በክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ እና የቦሎቄ ክላስተር፣ የቀበሌ አስተዳደር የስራ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር ያሉ ስራዎችን ጎብኝቷል።


ጉብኝቱን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ከፍያለው ተፈራ እንዳሉት፤ በጉጂ ዞን ተግባራዊ የተደረጉ የልማት ኢኒሼቲቮች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው ብለዋል።

በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኘው የስንዴ ምርት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ይህም የአርሶ አደሩን የስራ ባህል በመቀየር ከዚህ ቀደም ጾም ያድሩ የነበሩ መሬቶችን ወደ እርሻ በማስገባት ምርታማነትን በእጥፍ በማሳደግ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።


በተጨባጭ መሬት ላይ የሚታዩ ስራዎች ብልጽግና በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚረጋገጥ ማሣያ ናቸው ብለዋል።

የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ተግባራዊ ያደረጋቸው የተለያዩ ኢኒሼቲቮች በተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ነው ብለዋል።


ለአብነትም በጉጂ ዞን የተጎበኙት የስንዴ፣ የቡና፣ የማር እና ሌሎች ልማቶች ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።

የምስራቅ ጉጂ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ደስታ ገብረየስ ፤ በዞኑ በተያዘው የበልግ ወራት 258 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የዘር ዓይነት መሸፈኑን ገልጸዋል።

በዚህም ስንዴ፣ ቦሎቄና ሌሎች ሰብሎች መልማታቸውን ጠቁመው፤ ከዚህም 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።


የአርሶ አደሩ የሥራ ባህል በመቀየሩ ከዚህ ቀደም ጾም ያድሩ የነበሩ መሬቶችን ወደልማት ማስገባት መቻሉንም ጠቅሰዋል።

በጉጂ ዞን የሱሮ በርጉዳ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል በዳሳ ሚኤሳ እና ቴኔኮ ጂሎ ስንዴና ቦሎቄ በክላስተር በማምረት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።



የእርሻ መሬቶችን በአግባቡ በማልማት ምርታማነትን በማሳደግ ላይ እንደሚገኙ ገልጸው፤ ከዚህም በሚያገኙት ገቢ ህይወታቸውን እየቀየሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.