የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን በማቀድ እየፈጸመች ነው-ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

Jun 23, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካውያንን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን በማቀድና በመፈጸም ለፓን አፍሪካኒዝም መጠናከር ትልቅ ሚና እየተወጣች መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ


ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው "አርዳ የፖሊሲ ንግግር" መድረክ ላይ "ፖን አፍሪካኒዝምን ማጠናከር" በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል።


ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ማንሰራራት መልካም ዕድሎችና ፈተናዎች መኖራቸውን በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል።


አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ዓድዋ ላይ በተቀዳጀችው ድል በመነሳሳት የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴን በማቀጣጠል የራሳቸውን ሉዓላዊነት ማወጅ መቻላቸውን አውስተዋል።


ከዚህም ባለፈ በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ መሰረት የአፍሪካ ሕብረት እና ሌሎች ቀጣዊና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ተቋማትን ማቋቋም ተችሏል ብለዋል።


በአሁኑ ዘመን ድህነት፣ ኋላ ቀርነትና የእጅ አዙር የቅኝ አገዛዝ ተፅዕኖ የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ፈተናዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት በአፍሪካውያን ባህልና እሴት መቀረፅ አለበት ብለዋል።


ፓን አፍሪካኒዝም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተቋማዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች እንዳሉበት ገለጸው፣ አፍሪካዊ ችግሮች በአፍሪካዊ እውቀትና ጥበብ እንዲፈቱ የተጀመረው ጥረት ተስፋ ሰጭ መሆኑን ተናግረዋል።


አህጉራዊና ቀጣናዊ ትብብርን የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማጠናከርና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማፋጠን ያስችላል ያሉት ተጠሪ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ምሳሌ የሚሆን ሚና እየተወጣች ነው ብለዋል።


ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ አፍሪካውያን በራሳቸው እውቀት ፕሮጀክት አቅደው መገንባት እንደሚችሉ ትምህርት የሚሰጥና ቀጣናዊ ትብብርን በማጠናከር ለፓንአፍሪካኒዝም ማደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።


ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ እድገት ታሪክ የማይዘነጋቸው ትላልቅ አሻራዎች አኑራለች፤ ዛሬም ቀጥላለች ነው ያሉት።


የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍልስፍና ተቀይሯል ያሉት ተጠሪ ሚኒስትሩ፤ በሀገር በቀል የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሪፎርም የአፍርካን እሳቤ የሚያንጸባርቁ ለውጦች ተደርገዋል ብለዋል፡፡


በተለይም ከለውጡ ወዲህ በመደመር እሳቤ የጀመረቻቸው ሀገር በቀል የሪፎር ሥራዎች ለፓን አፍሪካኒዝም መጠናከርና ለአህጉራዊ ብልፅግና ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው የተግባር ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.