
ነገሌ ቦረና፣ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፦በጉጂ ዞን በመስኖ ከለማው መሬት ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአትክልትና ስራስር ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በዞኑ ከነሀሴ አጋማሽ እስከ ታህሳስ መጨረሻ የመጀመሪያው ዙር ከየካቲት መጀመሪያ እስከ ግንቦት መጨረሻ 2ኛ ዙር የመስኖ ልማት ወቅት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
የጽህፈት ቤቱ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ መንግስቱ ሂርባዬ፤ በዞኑ በ2ኛው ዙር የመስኖ ስራ 12 ሺህ 78 ሄክታር መሬት መልማቱን ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት በመሰብሰብ ለገበያ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው፥ እስካሁን በተካሄደው ስራም ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአትክልትና ስራስር ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
በመስኖ ከለሙት የአትክልትና ስራስር አይነቶች መካከል ድንች፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ጎመን፣ ቃሪያ፣ ካሮት፣ ቀይ ስርና ሰላጣ የመሳሰሉትን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡
ምርቱን ለማሳደግ 43 ሺህ 91 ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮና 1 ሺህ 626 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ፤16 ሺህ 803 ኩንታል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉን ጠቅሰዋል፡፡
በልማቱ ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን 23 ሺህ 797 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡
የመስኖ ልማቱን ምርታማነት ለማሳደግ ከማሳ ዝግጅት እስከ ምርት አሰባሰብ ባለው ሂደት የባለሙያ እገዛና ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...
May 15, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...
Apr 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...
Apr 17, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...
Apr 12, 2026