የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ግብር በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ለሀገር ልማት አስተዋጿቸውን እንደሚያጠናክሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ

Jun 5, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ለሀገር ልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንደሚያጠናክሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ።

"የብልጽግና ጉዟችንና የንግዱ ማኅበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ክልላዊ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።


በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል አቶ ሀብታሙ አሰፋ እንዳሉት የሀገርን ልማት በዘላቂነት ማስቀጠል የሚቻለው ግብርን በአግባቡ መክፈል ሲቻል ነው።

በመሆኑም በአካባቢያቸው ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነጋዴው ግብሩን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል ይኖርበታል ብለዋል።

እሳቸውም ግብር የመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ጌታቸው ክፍሌ ግብራቸውን በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ መንግስት ልማትን ለማጠናከርና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀዋል።

ግብርን በዘመናዊ መንገድ መክፈል እንዲቻል ለዲጂታል የአሰራር ሥርዓት ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

በሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ ጠንከር ያለ ቁጥጥር መደረግ አለበት ያሉት ደግሞ ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ሳህሌ ሰዋኮ ናቸው።

መንግስት ግብራቸውን በታማኝነት ከሚከፍሉ ነጋዴዎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መንቀሳቀስ እንዳለበትም ጠቅሰዋል።


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ በበኩላቸውቀጣይነት ያለው ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ በኃላፊነት መንፈስ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የውስጥ የገቢ አቅምን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የነጋዴው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተው፣ የግብር አሰባሰቡን ለማቀላጠፍ መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራ በቅንጅት እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት የሚቻለው ከሀዝብ በሚሰበሰብ ገቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግስት ፍትሀዊ የንግድ ውድድርን ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን እንዲወጣም አሳስበዋል።

መንግስት በሚሰበስበው ግበር በተለያዩ ዘርፎች ልማትን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

በተለይ ኢኒሼቲቭ ወስዶ በየሴክተሩ ባከናወናቸው የልማት ሥራዎች አመርቂ ውጤት እየተመዘገበና ዜጎችም ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.