አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25/2017(ኢዜአ)፦ የጌትስ ፋውንዴሽን የአፍሪካ 2063 አጀንዳን እውን ለማድረግ አጋዥ መሳሪያ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማይክሮሶፍት ባለቤትና የጌትስ ፋውንዴሽን መስራች ቢል ጌትስን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ታዳሚዎች በተገኙበት በአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከብሯል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የጌትስ ፋውንዴሽን በአፍሪካ ሩብ ክፍለ ዘመን ባስቆጠረባቸው ዓመታት በጤናው ዘርፍ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063ን የሚያስተጋባ የቀጣይ ስራቸው መመሪያ አድረገው እየተጠቀሙበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባትና በሽታን በመከላከል አምራች ወጣቶችን ለመፍጠር ወሳኝ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን በአፍሪካ መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማሟላት ያልተቋረጠ ድጋፍ ማድረጉንና ድካም አልባ ዓመታትን ማሳለፉን የገለጹት ምክትል ሊቀ መንበሯ፤ ለዚህም የአፍሪካ ሕብረት የላቀ አክብሮት አለው ብለዋል፡፡
በአፍሪካ የጤናውን ዘርፍ በፋይናንስ ለመደገፍና መድሃኒቶችና ክትባቶች በአፍሪካውያን አቅም እንዲመረቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም ገልጸዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን የአፍሪካ 2063 አጀንዳን እውን ለማድረግ አጋዥ መሳሪያ መሆኑን ገልጸው፤ ከአፍሪካ ጎን ስለቆሙ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ስኬት ፋውንዴሽኑ ጋር ያለውን ተሻጋሪ ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የማይክሮሶፍት ባለቤትና የጌትስ ፋውንዴሽን መስራች ቢል ጌትስ የአፍሪካን ምድር የረገጡት እንደአውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1993 እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡
አፍሪካ እምቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ በራሷ አቅም የተሻለ የጤና ስርዓት እንዲኖራት በጌትስ ፋውንዴሽን በኩል ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2012 በአፍሪካ የመጀመሪያውን ቢሮ አዲስ አበባ መክፈታቸውን ገልጸዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ፣ ኬንያና ሴኔጋል አድማሱን በማስፋት የአፍሪካን ጤናና መሰረተ ልማት ለማሻሻል መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በአፍሪካ በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶች እና የሚራቡ ህጻናት መኖር የለባቸውም ያሉት ቢል ጌትስ፤ የጤናና የትምህርት ስርዓቱን በማላቅ አፍሪካን ወደ ብልጽግና ማሻገር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሙሉ ጊዜያቸውን ድጋፍ በማድረግ እንደሚያሳልፉ ገልጸው፤ አብዛኛውን ሀብት በአፍሪካ ምድር ፈሰስ እንደሚያደርጉትም ቃል ገብተዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025