ጋምቤላ፤ ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል የመኸር እርሻ ልማቱን በማጠናከር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የታለመውን ግብ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሯ ከፌዴራልና ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በአኝዋሃ ዞን አቦቦ ወረዳ እየተከናወነ ያለውን የመኸር እርሻ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሯ በጉብኝቱ ወቅት ለኢዜአ እንደገለጹት በዘንድሮው የመኸር እርሻ ልማት የተጠናከረ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር መሬት ጦሙን እንዳያድር በትኩረት እየተሰራ ነው።
በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን ለአርሶና አርብቶ አደሩ በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትጋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም አርሶና አርብቶ አደሩን በማደራጀት፣ የኩታ ገጠም ግብርና ልማት ስራዎችን በማስፋት፣ ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረውን ጥረት በማጠናከርና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጡ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
በዕለቱ በአርሶና አርብቶ አደሩ ማሳ ላይ የተመለከቱት የመኸር እርሻ ልማት እንቅስቃሴ አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመስክ ምልከታው የነበሩት የግብርና ሚኒስትሩ አማካሪ ታረቀኝ ጽጌ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝቡን ኑሮ ለመለወጥና በምግብ ራስን ለመቻል እየተከናወነ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል፡፡
በተለይም አርሶ አደሩ በኩታ ገጠም እርሻ በመደራጀት እያከናወነ ያለው የግብርና ልማት ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል በመሆኑ መጠናከር ያለበት መሆኑን አክለዋል፡፡
አርሶ አደሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ያለው ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን በመስክ ምልከታው መረዳታቸውን ጠቅሰው ሚኒስቴሩ አርሶ አደሮቹ የሚያነሱትን የግብዓት ክፍተት ለመሙላት በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡
አርሶ አደር እስማኤል ሁሴን በሰጡት አስተያየት መንግስት አርሶ አደሩን በኩታ ገጠም እርሻ አደራጅቶ ወደ ልማት ካስገባ ወዲህ ተጠቃሚ እየሆንን ነው ብለዋል፡፡
ዘንድሮ መንግስት የእርሻ ትራክተርና ምርጥ ዘር በወቅቱ ስላቀረበ ካለፈው ጊዜ በተሻለ ማሳቸውን በዘር መሸፈናቸውን የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር አጉዋ ካን ናቸው፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025