አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪው በሰጠው ትኩረት አሁን ላይ ዘርፉ እየተነቃቃ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ገለፁ።
የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥና መዋቅራዊ ሽግግርን ለማምጣት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንዳሉት በዘርፉ የአሰራር ስርዓት ማሻሻያዎችና እንደ በአፍሪካና በቀጣናው ተወዳዳሪ የሚያደርግ አዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተዘጋጅቷል።
ማሻሻያውን ተከትሎ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የነበረበት የውጭ ምንዛሬ ችግር እንዲፈታ ያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
ከፌዴራል እስከ ክልልና ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሻሻልና የአምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ ችግሮች በቅንጅት እንዲፈቱ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ንቅናቄው ተዘግተው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ፣ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እንዲሻሻል፣ የገበያ እድል ለመፍጠርና አዳዲስ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።
ባለፉት ሶስት አመታት የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ46 በመቶ ወደ 61 ነጥብ 2 በመቶ ማደጉንም ነው ያስረዱት።
ተኪ የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውንና ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በአገር ውስጥ መተካት መቻሉን ገልጸዋል።
የአገር ውስጥ የገበያ ድርሻ ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 44 በመቶ ማደግ መቻሉንም ነው የተናገሩት።
የአገሪቱን እድገት ቀጣይነት ያለው፣ ተወዳዳሪና አስተማማኝ ለማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ለዚህም በዘርፉ ያለውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ እንደሚጠበቅ ተናግረው፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻል ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በሰጠው ትኩረት አሁን ላይ ዘርፉ እየተነቃቃ መሆኑን አብራርተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025